አማርኛ

ማሰላሰያ 76፦ ኢፍትሐዊ ውንጀላዎች

በጄምስ ቲሶ የተሣለው «የበጎው ወንበዴ ይቅር መባል»፣ በብሩክሊን ሙዚየም በኩል

ቪዲዮ

ምናልባት እያንዳንዱ ሰው በሌላ ሰው በግፍ ተወንጅሎ ያውቅ ይሆናል።  ይህም ሌላው ሰው ሆን ብሎ ሳይሆን፣ እውነታዎቹን ወይም የምናደርገውን ነገር ለምን እንደምናደርገው በስህተት ስለተረዳ ሊሆን ይችላል።  ወይም ደግሞ ይበልጥ ከተንኮልና ከጭካኔ የመነጨ ሊሆን ይችላል።  በሐሰት መወንጀል እጅግ የሚያሠቃይ ሊሆን ይችላል፤ በቁጣና ራሳችንን ለመከላከል በመሞከር ምላሽ እንድንሰጥም ሊፈትነን በጣም ይችላል።  ነገር ግን ለእንዲህ ያለ ከንቱ ነገር ተገቢው ምላሽ ምንድን ነው?  በእግዚአብሔር አሳብ ምንም ትርጉም በሌላቸው የማይረቡ ቃላት ራሳችንን ማድከም አለብን?  ምላሻችን የምሕረት መሆን አለበት።  በስደት መካከል ምሕረት ማሳየት። (ማስታወሻ #289 ይመልከቱ)።

በሕይወትዎ እንዲህ ያለ ግፍ ደርሶብዎት ያውቃል?  ሌሎች ስለ እርስዎ ክፉ ተናግረው እውነቱን አጣመው ያውቃሉ?  ይህ ሲከሰት እንዴት ምላሽ እንደሚሰጡ ያሰላስሉ።  ጌታችን እንዳደረገው እነዚህን ውንጀላዎች መቀበል ይችላሉ?  ለሚያሳድዱዎት መጸለይ ይችላሉ?  ይቅርታ ባይጠየቁም እንኳ ይቅር ማለት ይችላሉ?  በዚህ መንገድ ለመጓዝ ቆርጠው ይነሡ፤ ምክንያቱም በእግዚአብሔር ምሕረት መንገድ በመጓዝዎ ፈጽሞ አይጸጸቱም።

«አባት ሆይ፣ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው።»  ከመስቀል ላይ የተናገርካቸው ፍጹም የምሕረት ቃላትህ እነዚህ ነበሩ።  በጭካኔ እየተሳደድህ ሳለህ ይቅር አልህ።  ውድ ኢየሱስ ሆይ፣ ምሳሌህን እንድከተል፣ የሌላ ሰው ውንጀላ፣ ተንኮል ወይም ስደት ከአንተ እንዲያርቀኝ ፈጽሞ እንዳልፈቅድ እርዳኝ።  በሁሉም ጊዜ የመለኮታዊ ምሕረትህ መሣሪያ አድርገኝ።  ኢየሱስ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ።

ሃያ አራተኛ ቀን ማሰላሰያዎች፦
40 ቀናት በበረሃ & 40 ቀናት በመስቀሉ አጠገብ

ወደ ቅዱስ ዮሴፍ የሚቀርብ የዘጠኝ ቀን ጸሎት። ከማርች 10-18 ይጸለያል።

ለዐቢይ ጾም የሚረዱ ግብዓቶች

ለዐቢይ ጾም የመጽሐፍ ቅዱስ ማሰላሰያዎች

ተጨማሪ የእግዚአብሔር ምሕረት ማሰላሰያዎች

ዕለታዊ የወንጌል ማሰላሰያዎች

ማርች 17 – ቅዱስ ፓትሪክ፣ ጳጳስ

የዛሬ ቅዱሳን/በዓላት