ምስል ከፒክሳቤይ።
ብርሃን ጨለማን ያስወግዳል። በሳይንስ አንጻር ስንመለከት፣ ብርሃንና ጨለማ እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ ኃይሎች እንዳልሆኑ እናውቃለን፤ ይልቁንም ጨለማ ማለት ብርሃን አለመኖሩ ነው። ብርሃን ሲገባም ጨለማ ይጠፋል። የእግዚአብሔር ምሕረትም እንዲሁ ነው። ያለ ምሕረት ነፍሳችን ጨለማ ይውጣታል። ምሕረት በሌለበት ጊዜ በጥርጣሬ፣ በግራ መጋባት፣ በፍርሃትና በተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንወድቃለን። በዚህ ሁኔታ፣ የኃጢአት እድፍ ሊነግሥበት በሚችል ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እንቀራለን። እግዚአብሔር ግን የምሕረቱን ብርሃን ሊያመጣልን ይፈልጋል። ይህ ሲሆንና ነፍሳችንን ለዚህ ስጦታ ስንከፍት፣ የጥርጣሬ፣ የግራ መጋባት፣ የፍርሃትና የተስፋ መቁረጥ ጨለማ ይጠፋል። የምሕረት ብርሃን በሚኖርበት እነዚህ ሊቆዩ አይችሉም (ማስታወሻ ደብተር #831ን ተመልከት)።
ነፍስህን ስትመለከት ምን ታያለህ? ጨለማ አለባት? ጨለማው ያስከተለውን መጥፎ ውጤት ታያለህ? ጥርጣሬ፣ ግራ መጋባት፣ ፍርሃት ወይም ተስፋ መቁረጥ ታያለህ? ኃጢአት ታያለህ? እንዲህ ከሆነ፣ ጌታ እነዚህን ሸክሞች የሚያስከትለውን ጨለማ ለማስወገድና የምሕረቱን ብርሃን ለማብራት ይፈልጋል። ከሁሉ ይበልጥ ምሕረቱን የሚያስፈልገው በሚመስለው የነፍስህ ክፍል ላይ አሰላስል። ወደዚያ የሕይወትህ ክፍል ለመግባት እንደሚፈልግና እንድትፈቅድለት እየጠበቀህ እንደሆነ እወቅ። እንዲገባ እስክትፈቅድለት ድረስ ይጠብቅሃል።
ጌታ ሆይ፣ እባክህ ወደ ነፍሴ ጨለማ ግባ። ደማቅ የብርሃንህን ጨረሮች አብራ፣ ከአንተም ያልሆነውን ሁሉ አስወግድ። ጌታ ሆይ፣ ና፣ አድስና ብርታት ስጠኝ። ታላቅ ፍቅርህን እንዳይና እንዳውቅ እርዳኝ። ውድ ጌታዬ ሆይ፣ በምሕረትህ ብርሃን ውስጥ ለመኖር እመኛለሁ። ኢየሱስ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ።
የቅዱስ ልብ የዘጠኝ ቀን ጸሎት
የዘጠኝ ቀን ጸሎቱ እንዲደረግ የሚመከሩ ቀናት፦ ጁን 3 – 11, 2026
የእጅግ ቅዱስ ልብ ታላቅ በዓል ጁን 12, 2026 ነው።
ጁን 11 – ቅዱስ በርናባስ ሐዋርያ




