አማርኛ

አስተንትኖ 188፦ የጌታ ጥያቄዎች

የመልካሙ ሳምራዊ ምሳሌ፣ በበርሊሰን & ግሪልስ

ቪዲዮ

ጌታ አንድ ነገር እንድታደርግ ቢጠይቅህ፣ ምርጫ አለህን? «አይሆንም» ማለት ስለምትችል፣ ምርጫ አለህ። ይህም ኃጢአት ነው። ነገር ግን ክርስቶስን ለመከተል ከመረጥህና ግብህም መንግሥተ ሰማይ ከሆነ፣ ጌታ ከእኛ የሚጠይቀውን ሁሉ የማድረግ ግዴታ አለብን ማለት ተገቢ ነው። ጥያቄዎቹ የማያወላውሉና የማይለወጡ የፍቅር ትእዛዞች ናቸው። ከአቋሙ አይነቃነቅም። አይለወጥም። ይህን መቀበል የሚከብደን እልኸኞች ከሆንንና ለእርሱ ለመገዛት ፈቃደኞች ካልሆንን ብቻ ነው። ነገር ግን ከላይ እንደተገለጸው የፈቃዱን ባሕርይ ከተረዳን፣ በፍቅር ትእዛዞች ሲናገረን ግልጽና የማያሻማ ድምፁን ስንሰማ እጅግ ልንደሰት ይገባል። ፈቃዱንና ሕጉን በሕይወታችን ላለ ለእያንዳንዱ ችግርና ፍላጎት ፍጹም መልስ እንደሆኑ ልናይ ይገባል። የጌታ ጥያቄዎች መቀበል ያለብን ጥያቄዎች ናቸው። ከእነዚህ ጥያቄዎች አንዱም ሁላችንም ወደ ተትረፈረፈው ምሕረቱ እንድንገባና ለሌሎችም እንድናካፍለው መፈለጉ ነው (ማስታወሻ ደብተር #998 ተመልከት)።

ጌታችን ምሕረቱን ለሌሎች እንድታካፍል የሚጠይቅህን ጥያቄ አስተንትን። ይህን እንድታደርግ የሚጋብዝህ ብቻ አይደለም፤ ይህ የማይለወጥና የማይሻር ፍጹም ፈቃዱ ነው። ሐሳቡን ፈጽሞ አይለውጥም። ያለህ ምርጫ አንድ ብቻ ነው። በሕይወትህ ፈቃዱን ለመከተል ከመረጥህ፣ የመለኮታዊ ምሕረቱ ሰባኪ ለመሆን መስማማት አለብህ። ይህን ጥሪ ለመቀበል ፈቃደኛ ነህን? «አዎ» ለማለት ፈቃደኛ ነህን? ዛሬ በዚህ ጥያቄ ላይ አሰላስል፤ የእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ የማያወላውል መሆኑን የሚያንጸባርቅ ምርጫም አድርግ። ጌታችንን «አዎ» በለው፤ አትጸጸትም።

ጌታ ሆይ፣ ፈቃድህ ፍጹም ነው፤ የነፍሴም ደስታ ነው። በዓለም ውስጥ የመለኮታዊ ምሕረትህ መሣሪያ እንድሆን ስለጋበዝኸኝና ግዴታም ስለጣልህብኝ አመሰግንሃለሁ። ይህን ጥሪ በቅንዓት፣ በፍቅርና በትጋት እንድቀበል እርዳኝ። የተወደድህ ጌታ ሆይ፣ እንደ ፈቃድህ ተጠቀምብኝ። አንተን የማገልገል እጅግ ታላቅ ክብር ስለሰጠኸኝም አመሰግንሃለሁ። ኢየሱስ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ።

ለዓመቱ ተራ ዘመን የመጽሐፍ ቅዱስ ማሰላሰያዎች

ተጨማሪ የእግዚአብሔር ምሕረት ማሰላሰያዎች

ዕለታዊ የወንጌል ማሰላሰያዎች

የዛሬ ቅዱሳን/በዓላት