ማሰላሰል 233፦ የዝምታ ምላሽ
አንዳንድ ጊዜ በሕይወታችን ስለሚያጋጥመን ነገር ለእግዚአብሔር በግልጽና በዝርዝር መናገር ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ደጋግመህ፣ ደጋግመህ፣ ደጋግመህ መናገር እንዳለብህ ሊሰማህ ይችላል። እግዚአብሔርም ያዳምጥሃል…
365 ቀናት ከቅድስት ፋውስቲና ጋር
አንዳንድ ጊዜ በሕይወታችን ስለሚያጋጥመን ነገር ለእግዚአብሔር በግልጽና በዝርዝር መናገር ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ደጋግመህ፣ ደጋግመህ፣ ደጋግመህ መናገር እንዳለብህ ሊሰማህ ይችላል። እግዚአብሔርም ያዳምጥሃል…
ኢየሱስ ማዕበሉን ያረጋጋበትን ታሪክ አስታውስ (ማቴዎስ 8:23-27)። ይህ ተአምራዊ ድርጊት፣ በሕይወትህ በሚያጋጥሙህ ልዩ ልዩ ፈተናዎች መካከል ሰላም እንደሚያመጣልህ የሚያመለክት ትንቢታዊ ምልክት እንዲሆን ተደረገ…
የክርስቶስን ቁስሎች በማሰላሰል ፈጽሞ ልንታክት አይገባም። የደረሰበት እያንዳንዱ ቁስል ያለ አግባብ የተፈጸመበትና በሌሎች ኃጢአት ምክንያት የተከሰተ ነበር…
እግዚአብሔር በሕይወትህ ውስጥ ሕያው ሆኖ ይገኛልን? በውስጥህ ይኖራልን? ቀንና ሌሊት በልብህ ጥልቅ ውስጥ ከአንተ ጋር ይገኛልን? እግዚአብሔር እንዲተውህ የሚያደርግ አንድ ነገር ብቻ አለ፤ ይኸውም ለሞት የሚያበቃ ኃጢአት ነው…
ለሕይወታችንና ለእግዚአብሔር ክብር ታላቅ ነው ብለን የምንቆጥረውን ዕቅድ ማውጣት ለእኛ ቀላል ነው። ልናስብ፣ ልናቅድ፣ ነገሮችንም በተወሰነ መንገድ ልናዳብርና ልናደራጅ እንችላለን፤ በመጨረሻ ግን ያዘጋጀነው በእግዚአብሔር ሐሳብ ያለው እንዳልሆነ እንገነዘባለን…
ጌታችን ለሌሎች ፍጹም በሆነ ምሕረት የተሞላ ልብ ነበረው። ምሕረቱ አጠቃላይ ጽንሰ ሐሳብ ብቻ ሳይሆን፣ በተጨባጭ ድርጊት የሚገለጥ መሆኑን ልብ ማለት አስፈላጊ ነው…
ከሌላ ሰው ጋር ያለን ወዳጅነት የእግዚአብሔር ምሕረት ከሚፈስባቸው ኃይለኛ መንገዶች አንዱ ነው። ሆኖም ወዳጅነት በተለያዩ ደረጃዎች ሊኖር ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ይህ ትስስር ጥልቀት በሌላቸውና እምብዛም አስፈላጊ ባልሆኑ ነገሮች ላይ ይመሠረታል፤ በሌላ ጊዜ ደግሞ በጌታችን ውስጥ ጥልቅ መሠረት ይኖረዋል…
ከተለመዱት የሰው ዝንባሌዎች አንዱ ከመጠን በላይ መናገርና ራሳችንን ለሌሎች ማስረዳት ነው፤ በተለይም ድርጊቶቻችን በእነርሱ አስተሳሰብ ትክክል እንደሆኑ ለማሳመን እንጥራለን። ይህ በተለይ ሌሎች በተሳሳተ መንገድ እንደተረዱን ሲሰማን ይከሰታል። ኢየሱስ ግን ይህን ከሁሉ በላቀ ደረጃ አጋጥሞታል…
በሕይወት ውስጥ ምንም ነገር አስፈሪ መሆን አይገባውም። የምንታገሠውን እጅግ ከባድ ትግልና ሥቃይ እንኳ እግዚአብሔር በቀላሉ ለውጦ፣ የምሕረቱና የመቀደሳችን ምንጭ ሊያደርገው ይችላል…