ጀቡሎን፣ በዊኪሚዲያ ኮመንስ በኩል
አምላካችን የሆነውን ጌታችንን በእውነት ፈልገኸው ከሆነ፣ በልቡና በቅዱስ ፈቃዱ ውስጥ ይቀበልህ እንደሆነ ጠይቀው። ጠይቀው፣ አዳምጠውም። ሁሉን ለእርሱ አስረክበህ ራስህንም አቅርበህለት ከሆነ፣ እንደሚቀበልህ በመንገር ይመልስልሃል። አንዴ ራስህን ለኢየሱስ ከሰጠህና እርሱም ከተቀበለህ፣ ሕይወትህ ይለወጣል። ምናልባት ይለወጣል ብለህ በምትጠብቀው መንገድ ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን ተስፋ ካደረግኸው ወይም ከጠበቅኸው በላይ በሆነ መንገድ ለበጎ ይለወጣል (ማስታወሻ #14ን ተመልከት)።
ዛሬ በሦስት ነገሮች ላይ አሰላስል፦ 1) ኢየሱስን በሙሉ ልብህ ትፈልገዋለህን? 2) ራስህን ሙሉ በሙሉ ለእርሱ በመስጠት፣ ሕይወትህን ያለ ምንም ገደብ እንዲቀበል ኢየሱስን ጠይቀኸዋልን? 3) ኢየሱስ እንደሚወድህና እንደሚቀበልህ ሲነግርህ ለመስማት ራስህን ክፍት አድርገሃልን? እነዚህን ቀላል እርምጃዎች ተከተል፤ የምሕረት ጌታም ሕይወትህን እንዲመራ ፍቀድለት።
ጌታ ሆይ፣ በእውነት በሙሉ ልቤ እፈልግሃለሁ። አንተን እንዳገኝና እጅግ ቅዱስ የሆነውን ፈቃድህን እንዳውቅ እርዳኝ። ጌታ ሆይ፣ አንተን ሳገኝ፣ ሙሉ በሙሉ ያንተ እንድሆን ወደ መሐሪ ልብህ እንድትስበኝ እንድፈቅድልህም እርዳኝ። ኢየሱስ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ።




