ቪዲዮ
አንድ ትልቅ የበረዶ ቋጥኝ በሐሳብዎ ይሳሉ። አሁን በዚያ ቋጥኝ መካከል አንድ ውድ ሳንቲም እንዳለ ያስቡ። ያንን ሳንቲም ለማግኘት፣ የበረዶው ቋጥኝ መቅለጥ አለበት። ልባችንም እንዲሁ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ልቦች ከጊዜ ብዛት የተነሣ እጅግ ስለደነደኑ፣ የሰውየው እውነተኛ ዋጋና ክብር እንዲገለጥ እነዚያን ልቦች የማቅለጥ ዕድል እጅግ አነስተኛ ይመስላል። ኢየሱስ ግን ጨረሮቹ በታላቅ ኃይል የሚያበሩ ደማቅ ፀሐይ ነው። በቀጣይነት በእርሱ ፊት ሲቆዩ፣ እጅግ የደነደኑ ልቦች እንኳ ይቀልጣሉ (ማስታወሻ ደብተር #370 ይመልከቱ)።
በቀጣይነት በሚያሳየው የልብ ድንዛዜ ምክንያት «ተስፋ የቆረጡበት» ሰው ያውቃሉ? ዓመት ከዓመት ለመለወጥ ፈቃደኛ የማይመስል ሰው ያውቃሉ? ተስፋ አይቁረጡ። የእግዚአብሔር ጸጋና ምሕረት የሚያበሩበት የብርሃን መከፋፈያ ብርጭቆ ሆነው መኖርዎን ከቀጠሉ፣ እጅግ የደነደነው ልብ እንኳ ሊነካ እንደሚችል ይወቁ።
ጌታ ሆይ፣ ዛሬ በኃጢአታቸው እጅግ ለደነደኑት እጸልያለሁ። አንተ የሁሉንም ልብ ታውቃለህ፤ የሁሉንም ሐሳብ ታውቃለህ። እባክህ፣ መለኮታዊ ምሕረትህን እጅግ ወደሚሹት ምራኝ፤ የከበረና የሚያሞቅ ጸጋህ መተላለፊያ አድርገህም ተጠቀምብኝ። ኢየሱስ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ።
ሠላሳ ሦስተኛ ቀን አስተንትኖዎች፦
40 ቀናት በምድረ በዳ & 40 ቀናት በመስቀሉ አጠገብ





