አማርኛ

ማሰላሰል 94፦ ክፉውን መጋፈጥ

በዲያብሎስ የተፈተነው ክርስቶስ፤ በጆን ሪቶ ፔኒማን የተሣለ

ቪዲዮ

ከክፉው ኃይለኛ ጥላቻ ለመራቅ ከፈለግህ፣ ለቅድስና ከመትጋት ተቆጠብ። ሰይጣን አሁንም ይጠላሃል፣ ነገር ግን ቅዱስን ሰው የሚጠላውን ያህል አይጠላህም። እርግጥ ይህ ሞኝነት ነው! ማንም ሰው ከክፉው ጥላቻ ለመራቅ ሲል ከቅድስና ለምን ይርቃል? ወደ እግዚአብሔር ይበልጥ በቀረብን መጠን፣ ክፉው እኛን ለማጥፋት ይበልጥ እንደሚጥር እውነት ነው። ይህን ማወቅ መልካም ቢሆንም፣ የሚያስፈራ ነገር አይደለም። እንዲያውም ከክፉው የሚመጡ ጥቃቶች ለእግዚአብሔር ቅርብ መሆናችንን የሚያሳዩን ምልክቶች እንደሆኑ ልንመለከታቸው ይገባል (ማስታወሻ #412 ተመልከት)።

ዛሬ፣ ፍርሃት እንዳሸነፈህ የተሰማህባቸውን ማናቸውንም ሁኔታዎች አሰላስል። ብዙ ጊዜ ይህ ፍርሃት የክፉው ማታለያና ተንኮል በአንተ ላይ ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ የመፍቀድህ ፍሬ ነው። ፍርሃት በአንተ ላይ ተጽዕኖ እንዲያሳድር ከመፍቀድ ይልቅ፣ የሚጋፈጥህ ክፋት በእግዚአብሔር ያለህ እምነትና መታመን እንዲጨምር ምክንያት እንዲሆን ፍቀድ። ክፋት ወይ ያፈርሰናል፣ ወይም በእግዚአብሔር ጸጋና ኃይል እንድናድግ ዕድል ይሆንልናል።

ጌታ ሆይ፣ ፍርሃት ዋጋ የለውም፤ የሚያስፈልገው እምነት ነው። በየቀኑ በክፉው ጥቃቶች ከሚመጣ ፍርሃት ቁጥጥር ሥር ሳልሆን፣ በአንተ ረጋ ያለ ውስጣዊ ምሪት እንድመራ፣ እባክህ እምነቴን አብዛልኝ። ኢየሱስ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ።

አርባኛ ቀን ማሰላሰያዎች፦
40 ቀናት በበረሃ & 40 ቀናት በመስቀሉ ሥር

ሁለተኛ ቀን፦ ለእግዚአብሔር ምሕረት እሑድ ዝግጅት የሚደረግ የዘጠኝ ቀን ጸሎት

ለሳምንተ ሕማማት ተጨማሪ ይዘቶች

ለቅዱስ ቅዳሜ የጸሎት ማሰላሰያ

ተጨማሪ የእግዚአብሔር ምሕረት ማሰላሰያዎች

ዕለታዊ የወንጌል ማሰላሰያዎች

የዛሬ ቅዱሳን/በዓላት