አማርኛ

ማሰላሰል 99፦ የኃጢአት ግርፋት

የእሾህ አክሊል የደፋው ክርስቶስ፣ በዲርክ ቫን ባቡረን

ቪዲዮ

ኢየሱስ እንዲያ ያለ መከራ የተቀበለው ለምን ነበር? እንዲህ ያለ ከባድ ግርፋት ለምን ተገረፈ? ሞቱስ ለምን ያን ያህል አሠቃቂ ሆነ? ምክንያቱም ኃጢአት መዘዝ አለው፣ የከባድ ሥቃይም ምንጭ ነው። ነገር ግን ኢየሱስ ከኃጢአት ነጻ ሆኖ መከራን በፈቃዱ መቀበሉ የሰውን መከራ ለወጠው፤ በዚህም መከራ አሁን እኛን የማንጻትና ከኃጢአት እንዲሁም ከማንኛውም የኃጢአት ቁርኝት ነጻ የማውጣት ኃይል አለው (ማስታወሻ #445 ይመልከቱ)።

ኢየሱስ ያሳለፈው እጅግ ከባድ ሥቃይና መከራ በራስህ ኃጢአት ምክንያት እንደነበር ትገነዘባለህ? ትሑት እንድንሆን የሚያደርገንን ይህን እውነታ መቀበል አስፈላጊ ነው። በእርሱ መከራና በአንተ ኃጢአት መካከል ያለውን ቀጥተኛ ግንኙነት ማየት አስፈላጊ ነው። ይህ ግን የጥፋተኝነት ወይም የኀፍረት ስሜት ሳይሆን፣ የምስጋና ምክንያት ሊሆን ይገባል። ጥልቅ ትሕትናና ምስጋና።

ጌታ ሆይ፣ በቅዱስ ሕማምህ ስለታገሥኸው ሁሉ አመሰግንሃለሁ። ስለ መከራህና ስለ መስቀልህ አመሰግንሃለሁ። መከራን ስለዋጀህና የድኅነት ምንጭ እንዲሆን ስለለወጥኸው አመሰግንሃለሁ። የምታገሠው መከራ ሕይወቴን እንዲለውጥና ከኃጢአቴ እንዲያነጻኝ ለመፍቀድ እርዳኝ። ውድ ጌታ ሆይ፣ መከራዬን ከመከራህ ጋር አንድ አደርጋለሁ፤ ለክብርህም እንድትጠቀምበት እጸልያለሁ። ኢየሱስ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ።

ለፋሲካ ተጨማሪ ይዘቶች

ሰባተኛ ቀን፦ ለእግዚአብሔር ምሕረት እሑድ የዝግጅት ዘጠኝ ቀን ጸሎት

ተጨማሪ የእግዚአብሔር ምሕረት ማሰላሰያዎች

ዕለታዊ የወንጌል ማሰላሰያዎች

የዛሬ ቅዱሳን/በዓላት