አማርኛ

ማሰላሰል 28፦ የማማረር ፈተናዎች

ምስል ከNeedpix.com

ቪዲዮ

አንዳንድ ጊዜ ለማማረር እንፈተናለን።  እግዚአብሔርን፣ ፍጹም ፍቅሩንና ፍጹም እቅዱን ለመጠራጠር ስትፈተን፣ ይህ ፈተና ከዚያ የበለጠ ሌላ ነገር እንዳልሆነ እወቅ… ፈተና ብቻ ነው።  የእግዚአብሔርን ፍቅር እንድትጠራጠርና ጥያቄ ውስጥ እንድታስገባ በሚገፋፋህ በዚህ ፈተና መካከል፣ በእርሱ ያለህን መታመን አድስ፤ ለራስህ መራራትንም ተው።  ይህን በማድረግ ብርታት ታገኛለህ (ማስታወሻ #25ን ተመልከት)።

በዚህ ሳምንት ከሁሉ በላይ ያማረርክበት ጉዳይ ምንድን ነው?  እንድትቆጣ ወይም እንድትበሳጭ ከሁሉ በላይ የሚፈትንህ ምንድን ነው?  ይህ ፈተና ለራስህ ወደ መራራት ስሜት መርቶሃል?  በእግዚአብሔር ፍጹም ፍቅር ላይ ያለህን መታመን አዳክሞታል?  በዚህ ፈተና ላይ አሰላስል፤ በፍቅርና በበጎነት ለማደግ እንደሚረዳህ መንገድም ተመልከተው።  ብዙ ጊዜ ከሁሉ የሚከብደን ትግል፣ ወደ ቅድስና የሚያደርሰን ከሁሉ የላቀው መንገድ ተሰውሮ የሚገኝበት ነው።

ጌታ ሆይ፣ ስላማረርኩባቸው፣ ስለተቆጣሁባቸውና ፍጹም ፍቅርህን ስለተጠራጠርኩባቸው ጊዜያት አዝናለሁ።  ለራሴ በመራራት ስሜት እንድወድቅ ራሴን ስለፈቀድሁ አዝናለሁ።  ዛሬ እነዚህን ስሜቶች እንድተው፣ እነዚህንም ፈተናዎች በአንተ ይበልጥ ወደምታመንባቸውና ራሴን ወደማስረክብባቸው ጊዜያት እንድለውጣቸው እርዳኝ።  ኢየሱስ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ።

ጃንዩወሪ 28፦ ቅዱስ ቶማስ አኩዊናስ፣ ካህንና የቤተ ክርስቲያን መምህር—መታሰቢያ

ተጨማሪ የእግዚአብሔር ምሕረት ማሰላሰያዎች

ዕለታዊ የወንጌል ማሰላሰያዎች

ለዓመቱ ተራ ዘመን የመጽሐፍ ቅዱስ ማሰላሰያዎች

የዛሬ ቅዱሳን/በዓላት