አማርኛ

ማሰላሰያ 79፦ ብፅዕት የሐዘን እናታችን

በባለቀለም ብርጭቆ የተሠራ የስቅለት ሥዕል፣ ከNeedpix.com

ቪዲዮ

እናታችን ማርያም በሕይወቷ ብዙ መከራ ተቀብላለች።  አዳኟን በተአምር በፀነሰችበት ጊዜ ጥርጣሬንና ፌዝን ታግሣለች።  አምላክ የሆነው ልጇ ሲገፋና በትክክል ሳይረዱት ሲቀሩ፣ በፍጹም የእናትነት ፍቅር ተመልክታለች።  በስቃዩና በሞቱም ከጎኑ ቆማለች።  በዚህ ሁሉ ውስጥም የእናትነት ፍቅሯ ፍጹምና ብርቱ ነበር።  እኛም በሕይወታችን በምንቀበለው መከራ ሁሉ ከጎናችን ትቆማለች።  በርኅሩኅ ልቧም የፍቅርና የርኅራኄ ፍጹም ምስክርነት ትሰጠናለች (ማስታወሻ #315 ተመልከት)።

ዛሬ ስለ እመ አምላክ ልብ አሰላስል።  እውነተኛዋ የኢየሱስ እናት የሆነችው ብፅዕት እናትህ፣ ልጇን በሕይወቱ ዘመን ሁሉ እንዴት እንደወደደችው አሰላስል።  ልቧን ስፍር ቁጥር በሌለው ጊዜ የወጋውን የሐዘን ሰይፍ በአእምሮህ ሳል።  ልጇንም ሆነ እርሱን እንዲህ በጭካኔ ያንገላቱትን ሰዎች የወደደችበትን ፍጹምና ርኅሩኅ ፍቅር ለመረዳት ጣር።  ፍቅሯን እንድትመስል ዛሬ ጸሎቷን ለምን፤ ያንንም ፍቅር በብዛት በአንተ ላይ እንድታፈስስ ጠይቃት።  አታሳፍርህም።

እጅግ የምወድሽ እናቴ፣ ንግሥቴ ሆይ፣ እባክሽ ስለ እኔ ጸልዪ፤ የእናትነት እንክብካቤሽንም እንዳውቅ እርጂኝ።  ከንጹሕ ልብሽ የሚፈሰውን የምሕረት ብዛት እንድቀበል፣ በሁሉም ነገር ወደ አንቺ እንድዞር እርጂኝ።  ቸርነትሽንና ርኅራኄሽን እንድመስል፣ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸውም ሁሉ ጎን እንድቆም ጸጋን ስጪኝ።  እናታችን ማርያም ሆይ፣ ስለ እኛ ጸልዪ።  ኢየሱስ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ።

ሃያ ሰባተኛው ቀን ማሰላሰያዎች፦
40 ቀናት በበረሃ & 40 ቀናት ከመስቀሉ ሥር

ለዐቢይ ጾም የመጽሐፍ ቅዱስ ማሰላሰያዎች

ተጨማሪ የእግዚአብሔር ምሕረት ማሰላሰያዎች

ዕለታዊ የወንጌል ማሰላሰያዎች

ለዐቢይ ጾም የሚረዱ ግብዓቶች

የዛሬ ቅዱሳን/በዓላት