በቅዱስ ቁርባን ማሳያ ዕቃ ውስጥ በቅዱስ ቁርባን የሚገኘው ኢየሱስ፣ ከ needpix.com
በእጅግ ቅዱስ ቁርባን የሚገኘውን ክርስቶስ ምንም ያህል በጥልቅ ብንወደውና ብንሰግድለት፣ በቂ ሊሆን አይችልም። በእጅግ ቅዱስ ቁርባን በሚገኘው በእርሱ ፊት ስንሆን፣ ተሸፍኖ የሚገኘውን ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ማየት ይገባናል። እርሱ፦ ምሕረት፣ የዘላለም ሕይወት፣ ዘላለማዊው እግዚአብሔር፣ የኃጢአተኞች አዳኝ፣ ሕያው ውሃ፣ የንጹሕ ፍቅር እሳት፣ የሕመሞቻችን ሁሉ መድኃኒት፣ የፍቅር ስሜቶች ሁሉ፣ የሁሉ ተስፋ፣ ሸክሞችን የሚያነሣ ነው… በእርሱም ሙሉ በሙሉ ልንታመን የሚገባው ነው። (ይመልከቱ፦ የማስታወሻ መጽሐፍ #356)።
የተቀደሰውን ሕብስ ስትመለከት ምን ታያለህ? በዓይኖችህ እንጀራ ታያለህ፣ በነፍስህ ግን እግዚአብሔርን ማየት ይገባሃል። እግዚአብሔርን በክብሩና በኃይሉ ሙላት ማየት፣ በኃይልህም ሁሉ ለእርሱ መስገድ ይገባሃል። በቅዱስ ቁርባን ከሚገኘው ጌታችን ጋር ያለህ ግንኙነት እንዴት እንደሆነ አስብ። እግዚአብሔር አእምሮህን በእርሱ እውነተኛ እውቀት እንዲሞላውና ልብህን በሚነድ ፍቅር እንዲያነሣሣው ጸልይ።
ጌታ ሆይ፣ በእጅግ ቅዱስ ቁርባን የምትገኘውን አንተን እንዳውቅና እንድወድ እርዳኝ። በዚህ ቅዱስ ስጦታ አማካይነት የሚገኘውን የምሕረትህን ስጦታ እንድረዳ እርዳኝ። በዚህ በተቀደሰው ሕብስ በምትገኝበት ፊትህ በምቀርብበት ጊዜ ሁሉ ለአንተ መስገድን እማር። ኢየሱስ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ።
ሠላሳ አንደኛ ቀን ማሰላሰያዎች፦
40 ቀናት በበረሃ & 40 ቀናት በመስቀሉ አጠገብ
ማርች 25 – የጌታ ብሥራት




